ክፍል 1: የማህበሩ ስያሜ 

ይህ ማህበር  ፟የትውልደ ኢትዮጽያውያን ወንዶች ማህበር በአግደር ፟በመባል ይጠራል። 

ክፍል 2:የማህበሩ ዓርማ 

  • በሂደት ይጸድቃል ። 

ክፍል 3: የማህበሩ ዓላማ 

  1. በአባል ወይም በቤተሰቡ ላይ ሐዘን ሲደርስ የችግሩ ተካፋይ በመሆን መርዳት። 


  1. አንድ ዓባል ወይም ቤተሰቡ ቢታመም አስታማሚው በሚፈቅደው መንገድ ማገዝና ሊፈጠር የሚችለውን  የአስታማሚውን ጫና መቀነስ። 


  1. አባላትና ቤተሰብ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንዲቀራረቡና እንዲጠያየቁ ማድረግ።



 ክፍል 4: የማህበሩ አባል ስለመሆን 


  1. ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሆኖ እድሜው 18ና  ከዚያ በላይ ከሆነ አስፈላጊውን ክፍያመፈጸም ሙሉ አባል መሆን ይችላል። ይህም ማለት የአባልነት መመዝገቢያውንና የመጀመሪያውን ወር ክፍያ ያጠቃልላል። 


  1. ማህበሩ አባል ከሆነ ቤተሰብ ጋር እየኖረ 18 ዓመት የሞላው ሰው የማህበሩን መስፈርት አሟልቶ   በአባልነት መመዝገብ ይችላል። 


  1.  አንድ ሰው የዕድሩ ዓባል መሆን ከፈለገ የመተዳደሪያውን ደንብ አንብቦ ተረደቶ ሲያምንበት የአባልነት የማመልከቻ ፎርም ይሰጠዋል


  1.  አባል ለመሆን የሚፈልግ ሰው የአባልነት መጠየቂያ ፎርሙን ሞልቶ ለጽ/ቤቱ ማቅረብ 

      አለበት። የቤተሰቡን አባላት፣ እናት፣ አባት፣ እህትና ወንድም ስም ዝርዝር በፎርሙ ላይ   ይመዘግባል። 


  1.  አንድ ግለስብ ለማህበሩ አባልነት መመዝገብ የሚችለው ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው::

Comments